አርሶ አደሩ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን ተጠቅሞ በዓመት ከሶስት ጊዜ በላይ አምርቶ የምግብ ዋስትናውን በማረጋገጥ ከተረጂነት መላቀቅ እንዲችል ድጋፎችን ማጠናከር እንደሚገባ የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ ገለጹ!By lanfuro / November 15, 2025 ጦራ/ህዳር-6/2018 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ፣የመንግስት ዋና ተጠሪና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ፣የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ አብደላ አህመድ፣የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ሐላፊ አቶ ሙሀባ ረሺድ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ሐላፊ አቶ ኑርሰቦ አሰሞን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በወረዳው ቂቆራ ቀበሌ ከ70 ሄ/ር መሬት በላይ በማልማት 215 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦበተሰራው”የቂቆራ አነስተኛ ዘማነዊ የመስኖ”ፕሮጀክት ተገኝተው አሁን ላይ እየተከናወኑ ባሉ የበጋ መስኖ ተግባራት ላይ ምልከታ በማድረግ በመስኖ የሚለሙ የጓሮ አትክልትና ሌሎችንም ዘሮች አስጀምረዋል።አርሶ አደሩ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን ተጠቅሞ በዓመት ከሶስት ጊዜ በላይ አምርቶ የምግብ ዋስትናውን በማረጋገጥ ከተረጂነት መላቀቅ እንዲችል ከወትሮው በተለየ መልኩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን የገለጹት የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ በተለይም እንደዚህ አይነቶቹ ወጪና ጉልበት ቆጣቢ አነስተኛ ዘመናዊ የመስኖ አማራጮች ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከማጉላት አንጻር ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶ በአግባቡ መጠቀም ለግብርናው ምርት እድገት ድርሻው የጎላ ነውም ብለዋል።አቶ ሸምሴ ጉንዳ አክለው አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ የጸደይ እና የበጋ መስኖ ልማትና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከሌሎች ተግባራት አጣጥሞ በመምራት የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።ግብርና የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ያመለከቱት የላንፉሮ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ ከድህነት ጋር ላለመኖር አርሶ አደሩ ቁርጠኛ ሆኖ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን ተጠቅሞ በዓመት ከሶስት ጊዜ በማምረት ግብርናውን ዉጤታማ ማድረግ እንዲችል ድጋፍና ክትትሎችን በማጠናከር መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።አቶ ሸምሴ ሳዲቅ አክለው እንደገለጹት አርሶ አደሩ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን ተጠቅሞ በአመት ከሶስት ጊዜ በላይ አምርቶ የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ እንዲችል እየተደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደገ የመጣውን የስርዓተ ምግብና ገበያ ፍላጎት ለማሟላት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።በአለም አቀፉ የግብርና ልማት ትብብር ፈንድ/ኢፋድ/እና በወረዳው ህብረተሰብ በተገነባው አንስተኛ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክት የተለያዩ የጓሮ አትክልትና ሌሎችምን ሰብሎች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ አብደላ አህመድ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም.የበጋ ወቅት መስኖ ከ20 ሄ/ር በላይ መሬትን በዚህ የመስኖ ፕሮጀክት ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።በተለይም አሁን እየተስተወለ ላለው የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት አሁን ላይ እየተካሄደ ያለው የበጋ መስኖ ስራ ገበያ ተኮር ምርቶችን አምርቶ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እንዲሁም ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድልን በመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል አቶ አብደላ አህመድ።