በላንፉሮ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አዘጋጅነት የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎበኘት ተከበረ፡፡

ጦራ/መስከረም-21/2018 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/በዚህም የመስክ በዓል በወረዳው በረጴና ሉቄ ቁዱሳ ቀበሌዎች በአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላት፣በአርሶ አደሮችና በወጣቶች የተከናወኑ የዶሮ እርባታ፣የስንዴ፣የበቆሎ፣የቡና እና ሌሎችም ክላስተሮች ተጎበኝተዋል፡፡
የመስክ በዓሉ በግብርና ልማት ስራዎች፥በአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላት፣በአርሶ አደሮችና በወጣቶች የተከናወኑ ውጤታማ ተሞክሮዎች ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገንዝበው በቀጣይ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ያለመ ነው ተብሏል።
መርሃ ግብሩ ላይ የኢንተርፕራይዞች ዶሮ እርባታ፣የዶሮ መንደሮች፣የበቆሎና የስንዴ ክላስተሮች፣የሉቄ ቁዱሳ የአርሶአደር ማሰልጠኛ ማዕከል እና በቡና ልማት ተግባር የተሰማሩ አርሶ አደሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሞክሮዎቻቸውን ለመስኩ ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
የላንፉሮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ሐላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በህሬ ኮርመጣ አርሶ አደሩ በመስክ ምልከታ ተግባራት የታዩ ኢኒሼቲቮችንና አዳዲስ የአመራረት ተሞክሮዎችን ወደ ሁሉም አርሶ አደሮች በማስፈት በግብርናው ዘርፍ ለማሳካት የተጣሉ ግቦችን ከግብ ማድረስ ይገባል ብለዋል።
እንደ ወረደ በ45 ክላስተር 3 ሺህ 6 መቶ 32 ሄ/ር መሬት በበቆሎ እንዲሁም 2 ሺህ 8 መቶ 76 ሄ/ር መሬት በ48 ክላስተር በስንዴ መሸፈኑን የገለጹት የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ እንደ ሉቄ ቁዱሳ ቀበሌ በ3 ክላስተሮች 325 ሄ/ር መሬት በስንዴ መሸፈኑን ገልጸዋል።
አርሶ አደሩ የክላስተሪንግ አሰራር ዘዴን በመጠቀምና በሌሎች አርሶ አደሮች መካከል ያለውን የምርታማነት ልዪነት ለማጥበብ በኩታ ገጠም እርሻ እየተሰራ ባለው ስራ የዚህ የሉቄ ቁዱሳ ቀበሌ የተከናወነው የስንዴ ኩታ ገጠም/ክላስተር ማሳ አንዱ ማሳያ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በመስክ በዓሉ ላይ የላንፉሮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ሐላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በህሬ ኮርመጣ፣ የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ፣የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሙሀባ ረሺድ እና አቶ አብደላ አህመድን ጨምሮ ሌሎች የወረዳ አመራሮች፣የዘርፉ የግብርና ባለሙያዎች፣የቀበሌ አስተዳዳሪዎች፣ሞዴል አርሶአደሮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top