Background of organization

የላንፍሮ ወረዳ  አስተዳደር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 05 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን ወረዳው በለውጥ ጎዳና ውስጥ ከሚገኙ የዞኑ ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡የወረዳው መቀመጫ ጦራ ከተማ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ 39 ኪሎሜትር ርቀት  ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ ሆሳዕና በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 99 ኪ.ሜ እንዲሁም ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 182 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ወረዳው በ18 ቀበሌዎችና በሁላት ታዳጊ ማዘጋጃ ቤታዊ ከተማ የተዋቀረች ሲሆን በወረዳዋ ከ……. በላይ የሚጠጋ የህዝብ ብዛት አለት። በወረዳው የሚገኘው አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የስልጥኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው።በወረዳው የሚገኘው ማህበረሰብ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ይሁን እንጂ የተለያዩ ብሔርና ሃይማኖት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰላምና በፍቅር ተዋደውና ተከባብረው በጋራ የሚኖሩበት፤የአብሮነትና የአንድነት መገለጫም ነው ወረዳው።
በተለይም ወረዳዉን አቋርጦ የሚያልፈው ከቆሼ-ጦራ-ሚቶ-ወራቤ የአስፋልት መንገድ ተጠቃሚ መሆን መጀመር ወረዳው ቀድሞውንም ከነበረው ለኑሮ፣ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹና በባህሪው ሞቅ ያለ የህዝብና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተደምሮ የወረዳውን ሁለንተናዊ ለውጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን ይህም ወረዳው በሁሉም ዘርፍ ፈጣንና አስተማማኝ መዋቅራዊ ኢኮነሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበ በፈጣን ዕድገት መገስገስ እንድችል ትልቅ አቀም መፍጠር ችሏል፡፡
ለአብነት:-
በግብርና ኢንቨስትመንት
ለበጋ መስኖ ስራ የሚሆን ምቹ የአየር ንብረትና ለም መሬት በወረዳው ባሉ ብዙ ቀበሌዎች መኖሩ እንዲሁም በጸደይ የአዝመራ ወቅት በርካታ ሄክታር መሬትን በሽንቡራና በሌሎች ፈጥነው በሚደርሱ ሰብሎች በመሸፈን ውጤታማ መሆን መቻሉ፣ንብ ለማነብ፣ለማድለብ፣ለማሞከት፣ለወተት ላሞች እርባታ እና ለሌሎችም የግብርና ልማት ዘርፎች ምቹ ሁኔታ መኖሩ ወረዳውን ተመራጭ ያደርገዋል።
በቱሪዝም ዘርፍ:-የጡፋ ሐይቅ፣የባልጪና የወታንቦ ገቤ ሰንሰለታማ ተራሮችና የተፈጥሮ እጸዋቶች፣የአውሊያ ቆቶ፣የጭርጭሬ ምንጭ፣የዲረማንቾ ፋን፣የቂቆራ ሼህ መታሰቢያ መስጅድ፣የላንፉሮ ገባባ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎችም የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች የወረዳው ሁለንተናዊ ብልጽግና ተስፋዎች ናቸው።

 

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top